የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጫናና ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ በብራስልስ ተካሄደ

By Tibebu Kebede

November 16, 2021

 

አዲስ አበባ፣ህዳር 7፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን አሉታዊ አለም አቀፍ ጫናና ጣልቃ ገብነት በመቃወም በብራስልስ ከተማ በአውሮፓ ህብረት ቢሮ ፊት ለፊት ሠላማዊ ሰልፍ ተካሄደ።

የአውሮፓ ህብረት በሀገራችን ላይ የሚያደርገውን ያልተገባ ጫና በመቃወም በበርካታ መቶዎች የሚቆጠሩ ከቤልጂየም፣ ከሉግዘምበርግ ፣ከሆላንድ ፣ከፈረንሳይ፣ ከጀርመን ፣ከስዊዘርላንድ ፣ከጣሊያን እና ከስፔይን የተወጣጡ ኢትዮጵዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች በተገኙበት በአውሮፓ ኮሚሽን ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አካሂዷል:: የዪናይትድ ስቴስ ጣልቃ ገብነትና ጫናንም ተቃውመዋል።

ሰልፉ በቤልጂየም በሚገኙ የዳያስፖራ አድቮኬሲ ቡድን የተዘገጃ ሲሆን፣ አውሮፓ አቀፍ ለማድረግ ከየአገሮቹ የተውጣጣ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ በማዋቀር ሠፊ ዝግጅት የተደረገ መሆኑ ታውቋል::

በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮች እና ፖሰተሮች የቀረቡ ሲሆን ፣ ከተለያዩ የአውሮፓ አገሮች የተገኙ የዳያስፖራ ማህበረሰብ ተወካዮች እና ወዳጆች ጭምር መልእክት ማስተላለፈቸው ተገልጿል፡፡

በሠልፉ አዘጋጆች በጽሑፍ የተዘጋጀውንም ደብዳቤ ከአውሮፓ ኮሚሽን የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ተወካይ በሰልፉ ቦታ ተገኝተው መቀበላቸው መታወቁን ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን