Fana: At a Speed of Life!

ከፀጥታ አካላት ጋር የአካባቢያችንን ሰላም እየጠበቅን ነው- የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ህዳር 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃረሪ ከተማ ነዋሪዎች ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የአካባቢያቸውን ሰላም እየጠበቁ እንደሚገኙ ገለጹ፡፡
የሀረሪ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችም በከተማው ማህበረሰብ እየተከናወኑ የሚገኙ ሰላምን የማስጠበቅ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
‘እኔም የሰፈሬ ፖሊስና የሰላም ዘብ ነኝ’’ በሚል በተለያዩ ወረዳዎች የአካባቢያቸውን ሰላም ሲያስጠብቁ ያገኘናቸው ነዋሪዎች÷ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የአካባቢያችንን ሰላም እየጠበቅን እንገኛለን ብለዋል፡፡
ህብረተሰቡም መታወቂያ በሚጠየቅበት ወቅት ተገቢውን ትብብር እያደረገና አጠራጣሪ ነገሮች በሚገጥሙ ወቅትም ለፀጥታ አካላት አሳልፎ እየሰጠ መሆናኑን ተናግረዋል፡፡
በተለይም ወጣቱ በላቀ ተነሳሽነት የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የገለጹት ነዋሪዎቹ÷ ባከናወኑት ተግባርም ህገወጥ እንቅስቃሴና ተግባር እየቀነሰ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ነስሪ ዘካሪያ÷ የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ህብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም በንቃት እንዲጠብቅ ለማስቻል ውይይት በማድረግ ወደ ስራ ተገብቷል ማለታቸውን ከሃረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.