Fana: At a Speed of Life!

ለክተት አዋጅ ጥሪው የደቡብ ክልል ነዋሪዎች በከፍተኛ ስሜት ምላሽ እየሰጡ ነው

አዲስ አበባ፣ህዳር 7 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ሕወሓትን ለመደምሰስ ለተጠራው የክተት አዋጅ የደቡብ ክልል ነዋሪዎች በከፍተኛ ስሜት ምላሽ እየሰጡ እንደሆነ የደቡብ ክልል የመንግሥት ተጠሪ የሆኑት አቶ ጥላሁን ከበደ ገለጹ።
 
አቶ ጥላሁን ከበደ እንደሚሉት እንደ ደቡብ ክልል የህልውና ዘመቻው ጥሪ ከተላለፈ ጀምሮ ህዝቡ በከፍተኛ ስሜት የመከላከያ ሰራዊት ደጀን ከመሆን ባለፈ ልጁን፣ ወንድሙን እና እህቱን የመከላከያ ስራዊት አባል እንዲሆን እያደረገ ነው።
 
በተጨማሪም ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፍ የሚሆን በሁለት ሳምንት ውስጥ 282 ሚሊየን የሚጠጋ በገንዘብ እና በአይነት ማሰባሰብ ተችሏል ብለዋል።
የክተት ጥሪውን በመቀበል በራስ ስንቅ በራስ ሎጂስቲክ ወደ ግንባር መዝመት አለብን በሚል ከፍተኛ መነሳሳት ተፈጥሮ የተደራጀ ሰራዊት ወደ ግንባር ተሸኝቷል ብለዋል አቶ ጥላሁን።
 
አገር የማፍረስ ተልዕኮ ይዞ ወደ ጦርነት የገባው አሸባሪው ሕወሓት ሰርጎ ገቦችን በማስገባት በክልሉ ውስጥ ባሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ረብሻ እና ግርግር እንዳይፈጥር ማህበረሰቡ አካባቢውን በንቃት እየጠበቀ ነው ማለታቸውን ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.