Fana: At a Speed of Life!

በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የሚሰሩ ጋዜጠኞች ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ምን ይላሉ?

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የሚሰሩ ጋዜጠኞች ስለ ኢትዮጵያ እውነት እየመሰከሩ ነው፡፡

በዚህም በጌቲ ኢሜጅስና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በፎቶ ጋዜጠኝነት እየሰራ የሚገኘው ጀማል ካውንተስ እና ራስመስ ሶንድሪስ ስለኢትዮጵያ ሃሳባቸውን ይገልጻሉ፡፡

“ጋዜጠኛ ሆኜ ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ሄጃለሁ” የሚለው ጀማል ካውንተስ ÷ ከፈረንጆቹ 2007 ጀምሮ የነበረውን የምስክር ወረቀት ይዞ የመጣው በቅርብ ከነበረው የኮንግረስ ምስክር ወረቀት ሌላ መሆኑን ያነሳል።

ጋዜጠኛው በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ለጉብኝት እና ለስራ ይመላለሳል፡፡

በዚህም በትክክለኛው መንገድ ÷ ማለትም የምስክር ወረቀት ወይም ፍቃድ በማግኘት ወደኢትዮጵያ መግባት እንደሚቻል እራሱን እንደአብነት አድርጎ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል፡፡

“ሌሎች ጋዜጠኞችስ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት የሚያጋጥሟችሁ ችግሮች አሉ ወይ? ብሎ ይጠይቃል፡፡

ሌላው ራስመስ ሶንድሪስ ከዚህ በፊት በብዕር ስም የቀድሞውን መንግስት ሲተች እንደነበር ጠቅሶ፥ አሁን ያለውን መንግስት መተቸት ካስፈለገ በመተቸት እና እውነታውን ለዓለም በማስረዳት ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ዓለም እውነታውን እንዲያውቅ ማድረግ ይገባቸዋል ሲል ሃሳቡን አስፍሯል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.