Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሠራዊት ቀን የፊታችን የካቲት 7 ቀን ይከበራል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የመከላከያ ሠራዊት ቀን የካቲት 7 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚከበር ተገለጸ።

በዓሉ “የሀገራችንን ሉዓላዊነትና የሕዝባችንን ሠላም በፅናት እንጠብቃለን” በሚል መሪ ሃሳብ የሚከበር መሆኑን  የመከላከያ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በዓሉ ከሕብረተሰቡ ጋር በሚደረጉ ውይይቶች፣ በበጎ አድራጎት ስራዎች፣ በስፖርታዊ ውድድሮች፣ የሠራዊቱን ዝግጁነት በሚያሳዩ ወታደራዊ ሰልፎችና ትርዒቶች ታስቦ እንደሚውል ተመላክቷል።

ቀኑ እስከአሁን ሠራዊቱ የሄደባቸው ጉዞዎች የሚቃኙበት፣ ሕዝባዊ ወገንተኝነቱን በማረጋገጥም እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ ተልዕኮውን በጽናት ለመወጣት ያለውን ዝግጁነት የሚያሳይበት ነው ብሏል።

ሠራዊቱ የሕዝቡን ሠላም በጽናት ለመጠበቅ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በተጨማሪም የሠራዊቱ አባላት የሀገሪቷን ሉዓላዊነትና የሕዝቦችን ሠላም በጽናት ለመጠበቅ ቃላቸውን  የሚያረጋግጡበት መሆኑም ተመልክቷል።

ከሁሉም በላይ የሠራዊቱ አባላት የሀገሪቷን ሉዓላዊነትና የሕዝቦችን ሠላም በጽናት ለመጠበቅ ለሕዝቡ ቃል የሚገቡበት መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.