Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ አርሲ 52 የአሸባሪ ቡድን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ አርሲ ዞን ነጌሌ አርሲ ከተማ የአሸባሪ ቡድኑ ህወሃት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማ አስተዳደሩ የአስተዳደርና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ገለፀ።
በፀጥታ አካላት በተካሄደው ዘመቻ የትህነግ አሸባሪ ቡድን አባላት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 52 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን÷ የፅህፈት ቤቱ ሀላፊ ሳጅን ሙሉጌታ አረዳ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
እነዚህ ተጠርጣሪዎች የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የመከላከያ ሰራዊት የቀድሞ አልባሳት፣ ኤስ ኬ ኤስ የጦር መሳሪያ፣ 13 ጥይቶች፣ 1 የፖሊስ የዝናብ ልብስ፣ 1 የፖሊስ ጫማ፣ 3 ፓስፖርትና 50 የተለያዩ የባንክ ሂሳብ ደብተር ተገኝቶባቸዋል ነው የተባለው፡፡
በተጨማሪም 5 ቼክ፣ የተለያዩ የሞባይል አይነቶች፣ 1 ላፕቶፕ፣ 10 የካሜራ ታብሌት፣ 15 መንጃ ፍቃድ፣ 40 የተለያዩ የመታወቂያ ወረቀቶችና የተለያዩ የፅሁፍ ማስረጃዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቁመዋል።
በቢቂላ ቱፋ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.