የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ

By Meseret Awoke

November 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በደቡብ ሱዳን ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ተወያይቷል።

ተወያዮቹ የህወሓትን አፍራሽ ተግባር እና ከአንዳንድ የዓለም አቀፍ አካላት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ እየደረሰ ያለውን አላስፈላጊ ጫና አውግዘዋል።

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ÷ ህወሓት በኢትዮጵያ በተነሳ ተቃውሞ ከስልጣን መወገዱን ተከትሎ እየፈፀመ ያለውን የማተራመስ ተግባር አንስተዋል።

በተጨማሪም በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን 13 ሺህ ዶላር ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ የገቡትን ቃል አድንቀው ÷ በኢትዮጵያ ያሉ መልካም ተግባራትን እንደሚቀጥሉ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል ።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ለአገር ክብር ሲሉ ህይወታቸውን ለሰጡ የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ እንዲሁም ለአፋር ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!