Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ለሰራዊቱ ከ54 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አሰባሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ከ54 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መሰብሰቡን የክፍለ ከተማው አስተዳደር ገለጸ።
 
የክፍለ ከተማው ዋና አስፈፃሚ ወይዘሮ ሽታዬ መሀመድን ጨምሮ የክፍለ ከተማው አመራሮች ወረዳ 1 በነዋሪዎች እየተዘጋጀ ያለውን የስንቅ ዝግጅት ተመልክተዋል፡፡
 
የአገር መከላከያ ሰራዊትን ለመደገፍ እየተደረገ ባለው ርብርብ በክፍለ ከተማው በገንዘብና በቁሳቁስ ከ54 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መሰብሰቡን ወይዘሮ ሽታዬ ተናግረዋል፡፡
 
በድጋፍ አሰባሰቡ ሂደቱ ላይ እየተሳተፉ ላሉ የክፍለ ከተማው ማህበረሰብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ህብረተሰቡ ለመከላከያ ሰራዊታችን እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ እና ተደራጅቶ የአካባቢውን ሰላም የመጠበቅ ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መናገራቸውን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.