ኢመደኤ በማህበራዊ አገልግሎት ያደሳቸውን መኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎች አስረከበ
አዲስ አበባ፣ህዳር 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) በክረምት ማህበራዊ በጎ አገልግሎት ያደሳቸውን ሁለት የአረጋውያን መኖሪያ ቤቶች ዕድሳት አጠናቆ ለነዋሪዎች ዛሬ አስረክቧል፡፡
የኢመደኤ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንተነህ ተስፋዬ÷ ጳጉሜን 5 ቀን 2013 ዓ.ም ኢመደኤ የስጀመራቸውን የመኖሪያ ቤቶች ዕደሳ ግንባታ አጠናቆ ለነዋሪዎቹ ለማስረከብ በመብቃቱ ልዩ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡
ተነሳሽነትና ቀና አስተሳሰብ ካለ ብዙ መልካም ነገሮች መስራት ቀላል መሆኑን ያወሱት ዶ/ር አንተነህ÷በቀጣይም ከክፍለ ከተማውና ከወረዳው ጋር በመነጋገር የተለያዩ ማህበራዊ የልማትሥራዎች እንደሚሰሩ መናገራቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፎዚያ መሐመድ በበኩላቸው÷ እንዲህ ዓይነት ሰብዓዊነት የተሞላው መልካም ሥራ ተሠርቶ በማየታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!