ሀገር የመገንባት ሳይሆን የማፍረስ ታሪክ ያለውን አሸባሪ ቡድን አፍርሰን ደማቅ ታሪክ እንፅፋለን- አቶ ጃንጥራር አባይ
አዲስ አበባ፣ህዳር 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር የመገንባት ሳይሆን ሀገር የማፍረስ ታሪክ ያለውን አሸባሪ ቡድን አፍርሰን ልክ እንደ አባቶቻችን ደማቅ ታሪክ እንፅፋለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናገሩ፡፡
በመዲናዋ የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከማህበረሱ የተውጣጡ 10 ሺህ 800 የሰላም ሰራዊቶችን ያስመረቀ ሲሆን÷ በፕሮግራሙ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ምክትል ከንቲባው በሀገራችን ላይ ጥፋት እየፈፀመ ያለውን አሸባሪ ቡድን ለመመከት መላው ህዝብ ባለቤት ሆኖ ሀገሩን ለማዳን ዘምቷል፤ ውጤትም እያመጣ ነው ብለዋል፡፡
በአንድነትና በትብብር ለመከላከያችን ደጀን ሁነን ካስፈለገም ግንባር ድረስ ዘምተን የሽብር ቡድኑን ሀገር የማፍረስ አላማ አምክነን ሰላም ያላት ልደታ፣ ሰላም ያላት አዲስ አበባና ሰላም ያላት ኢትዮጵያን እንገነባለንም ነው ያሉት።
እኛ ኢትዮጵያዊያን ሽንፈትን አናቅም፤ የእኛ ታሪክ አሸናፊነት ብቻ ነው ለዚህም አባቶቻችን በአድዋ ያስመዘገቡት የድል ታረክ ህያው ምስክር ነው ያሉት ደግሞ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰግደው ኃ/ጊዮርጊስ ናቸው፡፡
ጠላትን ለመደምሰስ በየ ሰፈራችንና መንደራችን ደጀንነታችንን ማጠናከር አለብን ሲሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከክፍለ ከተማው ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People reached
0
Engagements