ህዝቡ ድጋፍ የሚያደርገው የአልደፈር ባይነት ሰሜቱን ለመግለፅ ነው – ሜ/ጀ ጥሩዬ አሰፌ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰራዊቱ ድጋፍ የሚያደርገው ለአገሩ ያለውን የአልደፈር ባይነት ስሜቱን ለማሳየት መሆኑን የመከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ ተናገሩ፡፡
የአራዳ ክፍለ ከተማ ሴቶች ፣ ህፃናት፣ ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ከአምስት ጋዜጠኞች ጋር በመተባበር 100 መቶ ኩንታል በሶ የስንቅ ዝግጀት አድርገዋል ፡፡
የመከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ በወቅቱ እንደተናገሩት ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰራዊታችን የሚያደርገው ድጋፍ የሚያስደንቅ ነው፤ ለግዳጅ አፈፃፀማችንም ትልቅ አቅም ይሆነዋል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰራዊታችን ድጋፍ የሚያደርገው ኖሮት ሳይሆን የአልደፈር ባይነትንና አንድነትን የሚያሳይ በመሆኑ ይህም ተግባር ሽብርተኛው ህወሓት እና ተላላኪዎቹ አስከሚደመሰሱ ድረስ ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል ፡፡
የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አባወይ ዮሐንስ በበኩላቸው ፣ ለሰራዊታን 39 ሚሊየን ብር ድጋፍ መደረጉን ጠቅሰው፥ አሁንም አካባቢያችንን እየጠበቅን በግንባር እየተፋለመ ላለው ሰራዊታችን በሎጅስቲክስ ለመደገፍ ይህንን ስንቅ አዘጋጅተናል ነው ያሉት።
ድጋፍ ያሰባሰቡት ጋዜጠኞች ለእናት አገራችንና ለሰራዊታችን የምናደርገው ደጀንነት ይቀጥላል ማለታቸዉን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!