Fana: At a Speed of Life!

ጠላትን ቀብረን የታሪካችንን ከፍታ እናስጠብቃለን – የቦረና ወረዳ ዘማች ወጣቶች

አዲስ አበባ፣ህዳር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአካል ስብራት ታክሞ ይስተካከላል፤ የታሪክ ስብራት ግን አንገት ስለሚያስደፋ ጠላትን ቀብረን የታሪካችንን ከፍታ እናስጠብቃለን ሲሉ የቦረና ወረዳ ዘማች ወጣቶች ተናገሩ።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በአማራ ላይ የሚያደርሰውን በደል ለአንድና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም ግፍ ያንገበገባቸው ዘማቾች ወደ ውጊያ እየተመሙ ነው።
ዘማቾቹ ጠላትን ድባቅ መትተው በአገርና በሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ ለመቋጨት እየከተቱ ነው ፤ ጠላትን ሳይደመስሱ እንደማይመለሱም በልበ ሙሉነት እየተናገሩ ነው።
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ያነጋገራቸው የደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ዘማች ወጣቶች ጠላትን ሳይደመስሱ ላይመለሱ መቁረጣቸውን ገልጸዋል።
የወረዳው ነዋሪ አማረ አዛናው ወጣቱ በሚችለው አቅም ሁሉ ጠላትን ለማጥፋት መነሳቱን ተናግሯል፤ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ የሚሉበት ምንም አይነት ምክንያት የለምም ብሏል።
ጠላትን ከሀገር ነቅሎ ለመጣል ሁሉም በየአደረጃጀቱ ቆርጦ መነሳቱን የተናገረው ወጣቱ በተባበረ ክንድ ጠላትን መምታት የሁሉም ወጣት ግዴታ መሆኑንም ገልጿል።
ሌላኛው ወጣት ሙሐመድ አብደላ በአደረጃጀታቸው መሠረት ጠላትን ድባቅ ለመምታት መውጣታቸውን ጠቁሞ ወሎ የገባውን ጠላት በገባበት እንደሚያስቀሩት ተናግሯል።
የአካል ስብራት ታክሞ ይስተካከላል፣ የታሪክ ስብራት ግን ትውልድን አንገት ስለሚያስደፋ ጠላትን ቀብረን የታሪካችንን ከፍታ እናስጠብቃለን ነው ያለው ወጣት ሙሃመድ።
ጠላትን ለማጥፋት በከፍተኛ እልህና ወኔ መነሳቱን የተናገረው ደግሞ ዘማች መምህር ሰለሞን አሰፋ ነው።
የጠላትን እንቅስቃሴ ማስቆም ካልተቻለና ካልተደመሰሰ በነፃነት መኖር አይቻልም፤ ነገ በነፃነት ለመኖር ዛሬ ላይ ጠላትን ድባቅ ለመምታት መዝመት ይገባልም ብሏል መምህር ሰለሞን።
ሁሉም ባለ አቅሙ ታግሎ ሀገሩን ነፃ ማውጣት ይገባዋል ሲል መልዕክት አስተላልፏል ሲል አሚኮ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
1 Share
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.