አሸባሪው ቡድን በአፋር ክልል ከ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት አውድሟል
አዲስ አበባ፣ህዳር 7 ፣2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአፋር ክልል ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች ህዝብን ለችግር በማጋለጥ ከ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማውደሙን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ቡድኑ ባደረሰው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተጎድተው ለችግር የተጋለጡ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ሰዎች እንደሚገኙ ተመልክቷል።
የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳይ ዙሪያ በሠመራ ከተማ እየተወያዩ ባሉበት መድረክ የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ መሀመድ ሁሴን ጉዳቱን አስመልክተው ለተሳታፊዎቹ እንዳብራሩት፤ ቡድኑ በክልሉ በከፈተው የእብሪት ጦርነት ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት አድርሷል።
በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በፈጸሙው ወረራ ከግለሰብ እስከ መንግስት ተቋማት ድረስ ከፍተኛ ውድመትና የንብረት ዘረፋ ማድረሱን አስረድተዋል።
የክልሉ መንግስት አሸባሪው ያደረሰውን ጉዳት ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ አባላት ያሉት ቡድን አዋቅሮ ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ከ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሃብትና ንብረት ውድመት ማስከተሉን አስታወቀዋል።
ከዚህም ውስጥ በቀዳሚነት በጤናው ዘርፍ ሆስፒታል፣ ጤና ጣቢያዎችና ጤና ኬላዎችን ጨምሮ ከ915 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ከሙሉ ግብአታቸው በአሸባሪው ተዘርፈዋል፤ወድመዋል ሲሉ ጠቅሰዋል።
በአርብቶ አደር ተቋማት ላይም ከ550 ሚሊዮን በላይ የሚገመት ውድመት ማስከተሉን አመልክተው፤ ከዚህም 39 የእንስሳት ጤና ኬላዎች፣ 4 የገበያ ማዕከላት እንዲሁም የተለያዩ 15 የውሃ ማቆር መለስተኛ ግድብ፣ 18 መለስተኛ የመስኖ አውታሮችና 40 የውሃ መጥለፊያ ፓምፖች ይገኙበታል።
ከግሉ ሴክተርም ከ15 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችና ከ2 ሺህ 100 በላይ የንግድ ተቋማት በአሻባሪው ቡድን ጥቃት ጥፋት እንደተፈጸመባቸው ገልጸዋል።
በተጨማሪ ከ83 በላይ ትምህርት ቤቶች ከውስጥ መገልገያዎቻቸው ጋር ጉዳት እንደደረሰባቸው ሃላፊው አመላክተዋል።
ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል ጭፍራ፣ጉሊና ያሎ ፣እዋና አውራ ወረዳዎች ይጠቀሳሉ ብለዋል።
አሸባሪው ቡድን በአጠቃላይ በክልሉ ወረራ በፈጸመባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ባደረሰው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተጎድተው ለችግር የተጋለጡ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች እንደሚገኙ አብራርተዋል።
የክልሉ መንግስትም ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማቶች ጋር በመሆን ለተጎጂዎች ከ52 ሺ በላይ ኩንታል ምግብ ነክ ድጋፎች ማድረጉን ያወሱት ሃላፊው፤ በቀጣይም መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በመተባበር ድጋፉ የሚቀጥል ይሆናልም ብለዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊ የሀገር ሽማግሌዎች መካከል አቶ ሀቢብ መሀመድ እንዳሉት፤ አሸባሪው የህወሃት ቡድን የንጹሃን ህይወት በማጥፋትና የሀገር ሃብት በማውደም የህዝብ ጠላትነቱን በግልጽ አሳይቷል።
ይህን አጥፍቶ ሊያጠፋን የመጣውን የሽፍታ ቡድን በቁርጠኝነት በመመከት ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ ወጣቶችን በማስተባበርና አካባቢያቸውን ነቅተው በመጠበቅ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።
ሌላው የሃገር ሽማግሌ አቶ ደርሳ አብደላ በበኩላቸው፤ የገጠመንን ክፉ ጠላት ህዝቡ ባለው ውስን ሃብት የሰራቸውን ጤና ጣቢያዎችንና ትምህርት ተቋማትን በማውደም ሊያንበረክከን አይችልም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People reached
148
Engagements
Boost post
141
1 Comment
6 Shares
Like
Comment
Share