ዋና ተግባራችን በጀትን በቁጠባ በመጠቀም ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ማድረግ ነው- አቶ አህመድ ሺዴ
አዲስ አበባ፣ህዳር 07 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር የዚህ አመት ዋና ተግባር የበጀት ሽግሽግ በማድረግ የመንግስትን በጀት በቁጠባ ለታለመለት አላማ እንዲውል ማድረግ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ገለጹ፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የ2014 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ 100 ቀናት እቅድ ዛሬ ህዳር 7 2014 ዓ.ም በሚኒስቴሩ መሰብሰቢያ አዳራሽ በቀረበበት ወቅት አቶ አህመድ ሺዴ እንደገለጹት፥ የመንግስትን ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበጀት ሽግሽግ በማድረግ በጀትን ያለምንም ብክነት በቁጠባ መጠቀም የዚህ አመት ዋና ተግባሩ መሆኑ አመልክተዋል፡፡
ከውጭ የሚሰባሰበው ሀብት አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የታለመውን ያህል ላይሳካ ስለሚችል በሀገር ውስጥ ታክስ አሰባሰብ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ሚኒስትሩ አሳስበው መንግስት ትኩረት ለሰጣቸው ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች እንደ አስፈላጊነታቸው ቅደም ተከተል በማውጣት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ መስሪያ ቤቶች የ2014 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ጥሩ እንደነበር አቶ አህመድ አመልክተው፥ የቀጣይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ100 ቀናት እቅድም በመንገስት አዲሱ የስራ አደረጃጀት መሰረት ባለተንዛዛ፣ ስራን ማእከል ባደረገና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ተግባራዊ እንደሚደረግም ተናገረዋል መናገራቸዉን ከሚኒዘቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን



0
People reached
29
Engagements
Boost post
24
5 Shares
Like
Comment
Share