ዓለምአቀፋዊ ዜና

በዓለም በኮቪድ 19 ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ5 ሚሊየን አለፈ

By Meseret Awoke

November 17, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ 19 ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ5 ሚሊየን 130 ሺህ በላይ አልፏል፡፡

እስካሁን ከ255 ሚሊየን 141 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ÷ ከ5 ሚሊየን 130 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በአንጻሩ ከ230 ሚሊየን 663 ሺህ በላይ ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውም ታውቋል፡፡

አሜሪካን ጨምሮ ህንድ፣ ብራዚል፣ ብሪታንያ እና ሩሲያ ቫይረሱ ከጸናባቸው አገራት መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡

ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽ በአፍሪካ ቫይረሱ ከተስፋፋባቸው አገራት መካከል ናቸው፡፡

ምንጭ ፡- ዎርልድ ኦ ሜትር

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!