Fana: At a Speed of Life!

ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ገለጸ።
የጽህፈት ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍቅርተ ታምር÷ አገሪቱ በህልውና ዘመቻ ላይ ብትሆንም ለግድቡ ግንባታ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።
 
በ2014 ዓ.ም በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ287 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን ጠቅሰው፥ ከዚህ መካከል 156 ሚሊየን የሚሆነው ከዳያስፖራ አባላት የተገኘ መሆኑን ተናግረዋል።
 
የተሰበሰበው ገንዘብ ከአገር ውስጥና በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በቦንድ ግዥና በድጋፍ መሆኑንም ገልጸዋል።
ሕዝቡ በሕልውና ዘመቻ ላይ ሆኖም ለግድቡ ግንባታ ድጋፉን በማጠናከር ለግንባታው መጠናቀቅ ቁርጠኝነቱን በተግባር አሳይቷል ብለዋል።
ግድቡ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ሁሉም ዜጋ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
ጽህፈት ቤቱ በተያዘው በጀት ዓመት 2 ቢሊየን ብር ለመሰብስብ አቅዶ እየሰራ ነው ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.