ቢዝነስ

በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው አንድሪያ ጫማ ምርቶቹን ለውጭ ገበያ ማቅረብ ጀመረ

By ዮሐንስ ደርበው

November 18, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው አንድሪያ ጫማ ምርቶቹን ለመጀመሪያ ጊዜ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ጀምሯል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ሳንዶካን ደበበ በትዊተር ገፃቸው አንዳሰፈሩት ኩባንያው ምርቶቹን “በኢትዮጵያ የተመረቱ” በሚል ነው ለገበያ ያቀረበው።

ኩባንያው የሴቶች ጫማ እያመረተ ለጣሊያን ገበያ እንደሚያቀርብ ተገልጿል።

ኩባንያው እስካሁን ለ230 ሰራተኞች የስራ እድል መፍጠሩ ታውቋል።