የሀገር ውስጥ ዜና

አገርን ከጥፋት ለመታደግ መዘጋጀታቸውን የብርሸለቆ ምልምል ሰልጣኞች አስታወቁ

By Feven Bishaw

November 18, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ዕዝ ሙዚቃ እና ቴአትር ቡድን በብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለ35ኛ ዙር ምልምል ሰልጣኞች የመድረክ ስራዎችን አቅርቧል፡፡

የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና አዘዥ ኮሎኔል ጌታቸው አሊ ወደ ማዕከሉ በመምጣት የኪነ-ጥበብ ድግስ ላዘጋጁ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡