ቴክ

በሰው በሚዘወር ፔዳል የሚበረው አውሮፕላን

By Alemayehu Geremew

November 18, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓን የሚገኝ ካናዛዋ የተሰኘ ኢኒስቲቲዩት ከካርበን ልቀት ነጻ የሆነ በሰው ሃይል (በፔዳል) የሚንቀሳቀስ አውሮፕላን ሰርቶ የተሳካ ሙከራ አድርጓል፡፡

በሙከራ ደረጃ የሚገኘው አነስተኛ አውሮፕላን ÷ የሚበረው እንደተለመደው በሞተር ኃይል ሳይሆን በሰው በሚዘወር ፔዳል እንደሆነም ተመላክቷል፡፡

የኢኒስቲቲዩቱ አጥኚዎች በሰው ኃይል የሚንቀሳቀሰውን አነስተኛ አውሮፕላን በጣም ቀላል ክብደት እንዲኖረው አድርገው ሰርተውታል።

https://www.facebook.com/watch/?v=610371933496295

ከዚህ ባለፈም አውሮፕላኑ ረዘም ያለ ርቀት እንዲበር ለማድረግ እየሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

አውሮፕላኑን ለመስራት ፎም እንጨት እና ፕላስቲክ ጥቅም ላይ ውሏል መዋሉን የቴክኖሎጂ መረጃዎችን የሚያጋራው ቸየፎሲ ባይትስ መረጃ ያመላክታል።