Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 አስተዳድር ነዋሪዎች ደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር ነዋሪዎች ደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉ ምግብ አልባሳትና የምግብ ማብሰያ ቁሳቁስን ያካተተ ሲሆን÷ የድጋፉ አስተባባሪ ቢንያም ተስፋዬ እንደገለጸው÷ ግምቱ 4 ነጥብ 5ሚሊየን ብር ይሆናል ተብሏል፡፡

ድጋፉ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እስኪመለሱ ይቀጥላል ያሉት የወረዳው ምክትል ስራ አስፈጻሚና የፋይናንስ ጽህፈት ቤት ሀላፊዋ ቤዛ ወርቅ አማረ ናቸው፡፡

ድጋፍን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደ አማኑኤል÷ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው በአንድነት ሆነን ስንደማመጥ እናሸንፋለን ብለዋል።

ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር ተሻግራ ህዝቦቿም ሰላማዊ ህይወት እንዲመሩ የሁላችንም ኢትዮጵያውያን መተጋገዝ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ህዝቡ ለተፈናቃይ ከሚያደርገው ድጋፍ ባሻገር በግንባር በመዝመት ጠላትን ድል ማድረግ አለብን ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በአላዩ ገረመው

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.