የብልፅግና ፓርቲ አባላት የአንድነት ፓርክን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብልፅግና ፓርቲ አባላት የአንድነት ፓርከን በዛሬው እለት ጎብኝተዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአዳማ ከተማ ላለፉት ቀናት ስልጠና እየወሰዱ መቆየታቸው የታወቃል።
ሰልጣኞቹ በቆይታቸው በተለያዩ ተግባራት ላይ ሲሳተፉ የቆዩት የፓርቲው አባላት፥ ችግኞችን መንከባከብ እና ጽዳት ካከናወኗቸው ተግባራት ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።
በአዳማ ስልጠና ላይ የቆዩት የፓርቲው አባላት በዛሬው እለት ደግሞ በታላቁ ቤተ መንግስት በመገኘት አንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል።
ፓርኩን የጎበኙ ከፍተኛ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በፓርኩ የተመለከቱት ነገር በሙሉ ባሉበት ኃላፊነት የሚጠበቅባቸውን በቁርጠኝነት እንዲሰሩ እንዳነሳሳቸው ተናግረዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ የአመራር ስልጠና ከጥር 16 ጀምሮ በአዳማ ከተማ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል።
ስልጠናው ፓርቲው ከኢህአዴግ ወደ ብልፅግና ሃገራዊ ውህድ ፓርቲ ከተሸጋገረ በኋላ በየደረጃው ለሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች በብልፅግና ፓርቲ ምንነትና አስተሳሰብ ዙሪያ የተዘጋጀ ነው።
ከዚህ ባለፈም በተጀመረው ሃገራዊ ለውጥና ከለውጡ ጋር ተያይዞ በተወሰዱ እርምጃዎች፣ በተገኙ ስኬቶችና የቀጣይ ስጋቶች ላይ አመራሩ የተግባር አንድነት እንዲኖረው ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑንም ተገልጿል።
በተጨማሪም ለሃገሪቱ ህዝቦች የለውጥ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አቅም ለመገንባትና ለቀጣይ ተልዕኮ ለማዘጋጀት ታስቦ የተዘጋጀ ነው መባሉም ይታወሳል።