Fana: At a Speed of Life!

በጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ንብረት ግምጃ ቤት ውስጥ ከ1 ሺህ 800 በላይ ጥይቶች ተያዙ

 

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ በንብረት ግምጃ ቤት ውስጥ የተቀመጡ ከ1 ሺህ 800 በላይ ጥይቶች በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ብርበራ ተያዙ፡፡

በቤተ ክህነቱ ግቢ በሚገኝ የንብረት ግምጃ ቤት በሚገኝ የፅህፈት እና የፅዳት እቃዎች ማስቀመጫ ውስጥ በተደረገው ብርበራ የተገኙት 1 ሺህ 363 የብሬን እና 493 የሽጉጥ ጥይቶች ናቸው፡፡

በተጨማሪም 2 የጥይት ማስቀመጫ ሳጥኖች እና 1 የክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ ካዝና ተይዟል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 1 ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገ ሲሆን÷ ህብረተሰቡ በስልክ፣ በአካል እና ሌሎች የመገናኛ አማራጮችን በመጠቀም እየሰጠ የሚገኘው ጥቆማ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

አሸባሪው ህወሓት ለሽብር ተግባሩ የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በተለያዩ የኃይማኖት ተቋማት ውስጥ ሲያከማች እና በኃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ግለሰቦችን በተላላኪነት እያሰማራ በበርካታ ንፁሃን ላይ አሰቃቂ እልቂት ሲፈፅም እንደቆየ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውሷል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.