ብዛት ያለው ወርቅና ጌጣጌጥ በህገ ወጥ መንገድ ተከማችተው ተያዙ
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከህብረተሰቡ የደረሰውን ጥቆማ መሠረት በመኖሪያ ቤታቸው በተደረገው ብርበራ ለጊዜው የዋጋ ግምታቸው ያልታወቀ አንድ ኪሎ ግራም ተኩል ወርቆችንና ስድሰት ኪሎ ግራም ተኩል የብር ጌጣጌጦችን ተከማችተው በመገኘታቸው ምርመራ እየተጣራ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ተጠርጣሪው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የአንድ ንግድ አክስዮን ማህበር ስራ አስኪያጅና የሌላ ንግድ አክሲዮን ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ ከመሆናቸው ውጭ በንግድ ሥራ የማይተዳደሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ህብረተሰቡ አካባቢውን በንቃት ከመጠበቅ ባሻገር የሚያያቸውን ማነኛውንም አይነት አጠራጣሪ ነገሮችን ለሚመለከተው የፀጥታ አካላት መጠቆሙን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አስተላልፏል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!