Fana: At a Speed of Life!

የጸረ-ተህዋስያን በጀርሞች መላመድ ችግርን ለመፍታት የሚያስችል ስትራቴጂክ እቅድ ጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጸረ-ተህዋስያን በጀርሞች መላመድ ችግርን ለመፍታት የሚያስችል የተለያዩ ሴክተሮች የተሳተፉበት የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ ጸድቋል።
የግብርና ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስቴር እንዲሁም የአካባቢና ደን ጥበቃ ኮሚሽን በጋራ “አንድ ጤና” በሚል “ኢኒሼቲቭ” ህይወት ያላቸው ፍጥረታትን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚያጠቁ በሽታዎችን ለመከላከል በርካታ ስራዎችን በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘም የጤና ሚኒስቴሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ እና የአካባቢና ደን ጥበቃ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ የጸረ-ተህዋስያን በጀርሞች መላመድ ችግርን ለመፍታት የሚያስችል የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ ተፈራርመው አጽድቀዋል።
እንደሀገር ከህዳር 9 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት “የጸረ-ተህዋስያን በጀርሞች መላመድ ችግርን ለመፍታት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት” ተብሎ እንደሚታሰብም ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.