በጎንደር አራዳ ክ/ከተማ ለህልውና ዘመቻው 28 ሚሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሠራዊት፣ ለልዩ ሃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አሥፈፃሚ አቶ ግዛቸው አሥናቀው እንደገለጹት÷ የሃብት ማሠባሠብ ተግባሩ የህልውና ዘመቻው ከተጀመረ አንስቶ በጥሬ ገንዘብ 21 ሚሊየን 564 ሺህ 615 ብር ተሰብስቧል።
ከዚህ ባለፈም ደረቅ ሬሽን፣ ብሥኩት፣ የተለያዩ አልባሣት፣ የንፅህና መጠበቂያ፣ ለህክምና የሚያገለግሉ ቁሳቁስና ውሃን ጨምሮ 7 ሚሊየን 210 ሺህ 928 ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ መሠብሠብ ተችሏል ነው ያሉት።
የክፍለ ከተማው ህብረተሠብ እንዲሁም ባለሃብቶች ተሣትፎ እጅግ የሚበረታታ ነው ያሉት አቶ ግዛቸው÷የህልውና ዘመቻውን በድል ለማጠናቀቅ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማሳሰባቸውን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!