ቢዝነስ

ምርት ገበያው በአራት ወራት የ4 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ምርት አገበያየ

By Feven Bishaw

November 19, 2021

 

አዲስ አበባ፣ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለፉት አራት ወራት 4 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር የሚያወጣ የግብርና ምርት ማገበያየቱን ገለጸ።

ምርት ገበያው በተጠቀሰው ጊዜ 51 ሺህ 640 ሜትሪክ ቶን ቡና፣ ሰሊጥ፣ አኩሪ አተር፣ አረንጓዴ ማሾ፣ የተለያዩ የቦሎቄ ዝርያዎች እና አምስት ቶን የርግብ አተር አገበያይቷል።