የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ረታ ዓለሙ ከእስራኤል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Meseret Demissu

November 19, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ረታ ዓለሙ ከእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በወቅቱም በአገራችን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታዎች እና የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚመለከት ምክክር አድርገዋል።

ፕሬዚዳንት ሄርዞግ እስራኤል እንደ ወዳጅ አገር ለኢትዮጵያ ያላትን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።

በውይይቱ ወቅትም ለኢትዮጵያ የአጋርነት መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!