የሀገር ውስጥ ዜና

የጌዴኦ ዞን ዲላ መስጂዶች ማኅበር ለተፈናቃይ ወገኖች የአይነት ድጋፍ አደረገ

By Alemayehu Geremew

November 19, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጌዴኦ ዞን የዲላ ከተማ መስጂዶች ማኅበር የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ተጎጂዎች የአይነት ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ ምግብ ነክ ፣ አልባሳትና የቤት መገልገያ ቁሳቁሶችን ያካተተ ሲሆን በ2 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ወጪ የተገዛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የጌዴኦ ዞን የዲላ ከተማ መስጂዶች ማኅበር ÷ ያቀረበውን እርዳታ ከአባላቱና ከማኅበረሰቡ ያሰባሰበው መሆኑን የማህበሩ አመራሮች በርክክቡ ወቅት ገልፀዋል።