Fana: At a Speed of Life!

ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን በሰሜን ሸዋለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ከወሎ ተፈናቅለው በሰሜን ሸዋ ዞን ለሚገኙ ወገኖች ግምቱ 1 ሚሊየን ብር የሆነ የምግብ ግብዓትና የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አዴረገ።
ድጋፋን ያስረከቡት የዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ንጉሴ መሸሻ ፥በትህነግ ሽብር ቡድን ወረራ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ የተቋሙ ስራ አመራርና ሰራተኞች የላኩት የዕለት ድጋፍ መሆኑን ገልጸዋል።
የህወሓት የሽብር ቡድን ሀገራችንን ለማፍረስ ከሚሰሩ የውጭና የውስጥ ጠላቶቻችን ጋር እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት ዶክተር ንጉሴ፥ በዚህም በሚሊየን የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል ብለዋል።
ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን የትህነግን እና አጋሮቹን እኩይ ሴራ በማጋለጥና ትክክለኛ መረጃን ለህዝብ ከማድረስ ባሻገር ለወገኑ ያለውን አጋርነት ለመግለጽ የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።
ድጋፋን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደ አማኑኤል ፥ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
ትህነግ ሀገር ለማፍረስ ከአጋሮቹ ጋር እየፈጸመ የሚገኘውን ክህደት በማጋለጥ ላይ ዋልታን ጨምሮ ሚዲያዎች የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
ግርማ ነሲቡ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.