የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ከ15 ሚሊየን ብር በላይ እና ሰንጋዎችን ድጋፍ አደረጉ

By Meseret Awoke

November 21, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኙ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 200 የሚጠጋ ሰንጋና ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።

ከየወረዳ እና ዞን ማዕከል የተሰበሰበቡ ሰንጋዎች ከጂንካ ከተማና ከወረዳ በተወጣጡ አመራሮች አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።

ድጋፉ ጂንካ ከተማን ጨምሮ ሁሉም ወረዳዎች እያንዳንዳቸው ከ10 እስከ 30 የሚሆን ሠንጋ በማዋጣት ነው በግንባር ለሚዋደቁና የኢትዮጵያን ህልውና ለማስጠበቅ ለሚተጉ ሠራዊት አባላት የተበረከተው።

ሁሉም ወረዳዎች ከሃሰተኛ መረጃ እንዲቆጠቡ አሳስበበው የጠላት ሀሰተኛ መረጃ ሰለባ እንዳይሆኑ ÷ አንድነታችን ተጠናክሮ ወደ ብልጽግና ከፍታ እንወጣለን ሲሉ ነው የገለጹት።

ከሠንጋና ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ ወደ ግንባር ድረስ ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ዳንሳ እንደገለፁት ÷ የዞኑ ማህብረሰብ 200 የሚጠጋ ሠንጋ፣ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ድጋ በተጨማሪ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚሆን የቀለብ ዝግጅት በማዘጋጀት ለሠራዊቱ እንዲደርስ ተደርጓል ማለታቸዉን ደሬቴድ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!