ኦስትሪያ ኮቪድ19 ማሻቀቡን ተከትሎ የእንቅስቅሴ ገደብ ጣለች
አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦስትሪያ እየጨመረ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት በአገር አቀፍ ደረጃ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሏን አስታወቀች።
የእንቅስቃሴ ገደቡ ለ20 ቀናት የሚቆይ ሲሆን፥ ከ10 ቀናት በኋላ እንደገና እንደሚገመገም ተገልጿል።
በክልከላዎቹ ምግብ ቤቶች እና አብዛኛዎቹ ሱቆች የሚዘጉ ሲሆን ትላልቅ ዝግጅቶች እንደሚሰረዙ ተገልጿል።
በተጨማሪም ከመሰረታዊ ወይም ወሣኝ ለሆኑ ጉዳዮች ውጭ ሰዎች ከቤታቸው እንዲወጡ አይፈቀድም።
ትምህርት ቤቶች እና የመዋዕለ ሕጻናት ማዕከላት ክፍት ሆነው የሚቆዩ ሲሆን፥ ወላጆች ልጆቻቸውን ቤት እንዲይዙ ይበረታታሉም ነው የተባለው።
ዓለም ላይ ኮቪድ-19 ከ257 ሚሊየን በላይ ሰዎች ሲያዙ ከ5 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።
ምንጭ፦ ቲ.አር.ቲ ዎርልድ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!