Fana: At a Speed of Life!

በአንድ ሳምንት ከ800 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሰባት ቀናት ብቻ ከ800 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ ድጋፍ መሰባሰቡን “የአይዞን ኢትዮጵያ” ዳያስፖራ ድጋፍ አስተባባሪ ገለጸ።

“አይዞን ኢትዮጵያ” ባለፉት 48 ሰዓታት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ የተሰባሰበውን የድጋፍ ገንዘብ ይፋ አድረጓል።

በቺካጎ እና ዳላስ ከ400 ሺህ ዶላር በላይ ሲሰበሰብ በሌሎች ግዛቶች ከተሰባሰበው የድጋፍ ገንዘብ ጋር በ48 ሰዓታት ውስጥ ከ500 ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰቡን አስታውቋል።

በዚህም ባለፉት ሰባት ቀናት የተሰበሰበው የድጋፍ መጠን ከ800ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ መድረሱን ነው የገለጸው።

ድጋፉን አጠናክሮ በማስቀጠል በቅርቡ ከ1 ሚሊየን ዶላር በላይ ለማሰባሰብ መታቀዱን “የአይዞን ኢትዮጵያ” የድጋፍ አስተባበሪ ማመልከቱን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.