የሀገር ውስጥ ዜና

የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የተቃጣውን አገር የማፍረስ አደጋ ለመመከት ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ

By Feven Bishaw

November 23, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ኢትዮጵያ” የሚለውን የነጻነት ስም የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለብን በሚል ያስተላለፉትን መልዕክት ተከትሎ ነው ከፍተኛ አመራሩ ዝግጁነቱን ያስታወቀው፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ትናንት ባካሄደው ስብሰባ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጦር ግንባር በመገኘት ጦሩን ለመምራት እንደሚሄዱ አስታውቀው በዛሬው ዕለትም ወደ ግንባር ተጉዘዋል፡፡