የሀገር ውስጥ ዜና

የግብርና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ለተፈናቃዮች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

By Feven Bishaw

November 23, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በአፋር ክልል በህወሓት ጁንታ ወረራ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ የምግብ ፣ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁስና የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን በክልሉ እንስሳት እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ በኩል ለክልሉ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤት አስረክበዋል።