የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች 11ኛ ክልል መሆን የጀመርነውን የለውጥ ጉዞ ያሳያል – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

By Meseret Awoke

November 24, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች 11ኛ ክልል መሆን የጀመርነውን የለውጥ ጉዞ የሚያሳይ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት እንዳሉት ÷ ኅብረ ብሔራዊነት አንድነትን የማጽኛ ዕሴት ነው።

ፌዴራላዊ ሥርዓት ሕዝብ ራሱን በራሱ እያስተዳደረ ሀገር የሚገነባበት ሥርዓት መሆኑን ገልጸው ÷ ይህንን በተግባር አሳይተናል ብለዋል።

’’ሰላማዊ፣ ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ሕገ መንግሥታዊ መብታችሁን ተጠቅማችሁ፣ 11ኛውን ክልል ለመሠረታችሁ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች እንኳን ደስ አላችሁ’’ ብለዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!