የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ‘ጠፋች ተበተነች’ ሲሏት ከአለት የጠነከረ አንድነት ገንብታ የምትኖር ናት – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

By Meseret Awoke

November 24, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ‘ጠፋች ተበተነች’ ሲሏት ከአለት የጠነከረ አንድነት ገንብታ ተከብራ የምትኖር አገር መሆኗን የስራ ፈጠራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡

ሚኒስትሯ እንዳሉት ÷ ኢትዮጵያ የውስጥ ተላላኪዎችና የውጭ ሴረኞች በደገሱት የጥፋት ድግስ በሸረቡት ሴራ ተጠልፋ የምትንኮታኮት ሳትሆን ሞተው ሊያኖሯት በቆረጡ እልፍ ልጆቿ ‘ወደቀች’ ሲሏት ቀና ቀጥ የምትል ፍሬ የምታፈራ ፤ ‘ጠፋች ተበተነች’ ሲሉ ከአለት የጠነከረ አንድነት የምትገነባና የምታፀና ነፃ የነበረች፣ ነፃ የሆነች፣ ነፃ ሆና ታፍራና ተከብራ የምትኖር አገር ናት፡፡

“ይህ ዕውን እንዲሆን ወቅቱ የሚጠይቀውን ጥበብ አንድነታችንን አጥብቀን መጠበቅ፣ በየቦታው የሚኖሩ እንቅስቃሴዎችን በንቃት መከታተል፣ ከከፋፋይ ሀሳቦችና ከሀሰት ፕሮፖጋንዳዎች መጠበቅ፣ በማህበራዊ ሚዲያ የምናጋራቸውን ምስሎችና መረጃዎች መጠንቀቅ በተሰማራንበት መስክ ውጤታማነታችንን በማረጋገጥ በእሾህ የታጠረ የሚመስለውን የሴራ አጥር በጣጥሰን ቀና ፤ ከፍ የምንልበት ቀን ቅርብ ነውም” ብለዋል፡፡

አክለውም ÷ እኛም የአባትና የእናቶቻችን ልጆች ነን ፤ ግን አያውቁንም ፤ እንበርታ ፤ እንፅና ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!