Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን አሁን የገጠማት ፈተና በታሪክ ከገጠሟት ሁሉ የተለየ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ በወቅታዊ እና ነባራዊ የሀገሪቱ ሁኔታ ዙሪያ መክረዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ በሚመለከት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አማካኝነት የውይይት መነሻ ሃሳብ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡
በውይይት መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ÷ ኢትዮጵያ አሁን የገጠማት ፈተና በታሪክ ከገጠሟት ሁሉ ለየት ያለ ነው ብለዋል፡፡
የራሷ ባንዳ ልጆች ከውጭ ጠላቶች ጋር በማበር እየወጓት መሆኑ ፈተናውን አስቸጋሪ አድርጎታል ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያዊ ውብ እሴታችን የሆነውን ሽምግልናን ያረከሰው፣ ለሀይማኖት አባት እና ቤተ እምነት ብሎም ለይቅርታ እና ምህረት ቦታ የሌለው አሸባሪው ህወሓት በትዕቢት እና እብሪት ተወጥሮ ወደ ጦርነት እንድንገባ አድርጎናል ሲሉ ተናግረዋል ወ/ሮ አዳነች፡፡
ሀገር አሁን ከገባችበት የሕልውና አደጋ ለመውጣት የሁሉም ርብርብ ያስፈልጋል ያሉት ከንቲባዋ÷ ለኢትዮጵያ መክፈል ያለብንን ሁሉንም ነገር ልንከፍል ይገባልም ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያን ማትረፍ ግድ ይላል ያሉት ከንቲባዋ ÷ የሃይማኖት አባቶችም በጸሎት እና በሚቻለው ሁሉ ድጋፍ በማድረግ የድርሻ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማሳሰባቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.