የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ የሚገኙ የትምህርት ማህበረሰብ አባላት ለተፈናቃዮች 50 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረጉ

By Meseret Awoke

November 25, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስአበባ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ የትምህርት ማህበረሰብ ክፍሎች ተፈናቅለው በደብረብርሃን ከተማ ለሚገኙ ወገኖች 50 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አበረከቱ።

ድጋፉን ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ እንዳሉት፥ በአዲስ አበባ የሚገኙ ከትምህርት ማህበረሰብ የተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ የምግብ ግብዓቶች ፣ የተማሪዎች ቁሳቁስ፣ የንጽህና መጠበቂያዎችን አካቷል። የተከፈተብን ጦርነት እንደ አገር በመሆኑ በጋራ ጠላታችንን እንመክታለን ተብለዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደ አማኑኤል በበኩላቸው፥ ለተደረገውን ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በዞኑ300 ሺህ ተፈናቃይ በመኖሩ ድጋፎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርባቸው አመላክተዋል።

በሰላማዊት ሙሉነህ

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!