Fana: At a Speed of Life!

የኢሶዴፓ እና የእናት ፓርቲ አመራሮች ለህልውና ዘመቻው ስኬት የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሶሻል-ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) እና የእናት ፓርቲ አመራሮች በግንባር በመሰለፍ ጭምር ለህልውና ዘመቻው ስኬት የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ አረጋገጡ፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በህልውና ዘመቻው ተሳትፎ በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላቀረቡት ጥሪ ምላሽ እንዲሰጥም ነው ፓርቲዎቹ ጥሪ ያቀረቡት፡፡

ፓርቲዎቹ ለፋና ብሮድካስቲንግበ ኮርፖሬት በላኩት መግለጫ ÷ የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ግንባር ዘምተው የህልውና ዘመቻውን ለመምራት መንቀሳቀሳቸው ተገቢና ወቅቱን የጠበቀ ውሳኔ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ ለህልውና ዘመቻው ስኬት ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብሎ ፓርቲያቸው እንደሚያምንም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ አንጻር የፓርቲያቸው አባላትና ደጋፊዎች ለዚሁ ዘመቻ ስኬት ተግባራዊ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን የአገራቸውን ህልውና ማስጠበቅ የሚችሉት ታግለው በማሸነፍ ብቻ መሆኑን በመገንዘብ በህልውና ዘመቻው ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢሶዴፓ እና እናት ፓርቲ አመራሮች በግንባር በመሰለፍ ጭምር ለህልውና ዘመቻው ስኬት የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ በላኩት መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡

በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን የውጭ ጫና እና የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻ አጥብቀው እንደሚያወግዙትም አስታውቀዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.