የአሮሚያ ክልል ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ሰንጋዎችን አስረከበ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉ የድጋፍ ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ብርሃኑ ፈይሳ ክልሉ ከሁሉም ዞኖች የተውጣጡ 1 ሺህ 100 የእርድ ሰንጋዎች ድጋፍ ማድረጉን ገልፀዋል፡፡
እስካሁን ድረስ በተደረጉ ዙሮችም ከ340 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን ነው ሰብሳቢው ያብራሩት፡፡
የአሮሚያ ክልል ሴቶች አደረጃጀትም ግምቱ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የአይነት ድጋፍ አድርጓል ነው የተባለው፡፡
የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ÷ ያለማንም ቀስቃሽ በራሱ ተነሳሽነት የሃገራችንን ህልውና እናረጋግጣለን በማለት ደጀንም ዘማችም በመሆን ህዝባችን ለሚያሳየው የጀግንነት ተግባር እጅግ የላቀ ምስጋና አለኝ ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!