የሀገር ውስጥ ዜና

የጋሞ ልማት ማህበር ከ39 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ የልማት ተግባራት አከናውኗል

By Feven Bishaw

November 28, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የጋሞ ልማት ማህበር በ9 ወራት ከ39 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ተግባራት ማከናወኑ ተገለፀ፡፡

የልማት ማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ትግሉ ኃይሌ÷ በ 9 ወራት ልማት ማህበሩ ቁልፍ የልማት ክፍተቶችን ለመሙላት በቅርንጫፍ እና በዋናው ልማት ማህበር 39 ሚሊየን 85 ሺህ 245 ብር ወጪ የተለያዩ የልማት ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል ።