Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

የብሄር ብሄረሰቦች አውደ ርዕይ የመክፈቻ ስነ ስርአት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ15ኛው የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት የብሄር ብሄረሰቦች አውደ ርዕይ የመክፈቻ ስነስርአት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተካሄደ፡፡ “ህብረ ብሔራዊ አንድነትና እኩልነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ቀኑ የሚከበር…

የህወሓት ቡድን ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ህገ-ወጥ ተግባር ፈፅሟል – አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህወሓት ቡድን ከሃገራዊ ለውጡ በፊትና በኋላ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ክልላዊ ምርጫን ጨምሮ የተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባር መፈፀሙን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ ገለጹ። አፈ ጉባኤው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ቡድኑ ህገወጥ ድርጊቱን…

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ መሰጠት ጀመረ 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ በ156 የመፈተኛ ጣቢያዎች 73 ሺህ 45 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ፈተና እየወሰዱ ነው፡፡ ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች አማርኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ሂሳብ፣ ባዮሎጂ ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣…

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ለተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮችና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮችና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርክ ሎውኩክ ጋር ተወያዩ፡፡ ውይይቱ የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ በሚሆንበት አግባብ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር ተብሏል፡፡፡…

15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በአዲስ አበባ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)15ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ተከበረ። በዓሉ “እኩልነትና ህብረ ብሄራዊነት ለጋራ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ነው ተከብሮ የዋለው። በበዓሉ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ…

15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በዓል በባህርዳር ከተማ በውይይት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በዓል ኢ-ህገመንግስታዊ እንቅስቃሴን ማስቆምና የህግ ማስከበር ተልዕኮ ለህብረ-ብሄራዊ አንድነታችን ያለው ፋይዳ በሚል መሪ ቃል በባህርዳር ከተማ በውይይት እየተከበረ ይገኛል፡፡ በውይይቱ የመከላከያ፣ የአማራ ልዩ…

በደሴ በ591 ሚሊየን ብር የአስፓልት መንገድ ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደሴ ከተማ በ591 ሚሊየን ብር ወጪ የአስፓልት መንገድ ግንባታ ስራ ተጀመረ። የከተማው ቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ መከተ ዘውዱ የመንገድ ግንባታ ስራውን አስጀምረዋል። በከተማ አስተዳደሩ ወጪ የሚገነባው የ7 ነጥብ 8 ኪሎ…

ዶ/ር ሂሩት ካሳው ከእስራኤል የዳያስፖራ ኢሚግሬሽንና የትብብር ሚኒስትር ታማኖ ሺታ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ከእስራኤል የዳያስፖራ ኢሚግሬሽንና የትብብር ሚኒስትር ታማኖ ሺታ ጋር ተወያይተዋል። ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው ሁለቱ ሀገራት ባላቸው ጥብቅ ትስስር ረጅም ታሪክ ማስመዝገባቸውን…

አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለካናዳ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ከሰሃራ በታች ምክትል ሚኒስትር ገለጻ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ለካናዳ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ከሰሃራ በታች ምክትል ሚኒስትር ማላ ካሃና ገለጻ አደረጉ፡፡ አምባሳደር ናሲሴ በወቅቱም በመንግስት በትግራይ ክልል…

በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ኒውክሌርን ለሰላማዊ ዓላማ ማዋል ስምምነት ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ኒውክሌርን ለሰላማዊ ዓላማ ማዋል ስምምነት ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ። አዋጁ የጸደቀው ዛሬ በተካሄደው 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ ነው፡፡…