Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 164 ሺህ በላይ ደርሷል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 164 ሺህ 610 ደርሷል። ከአራት ወራት በፊት በቻይና ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ የተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አሁን ላይ ከ190 በላይ በሚሆኑ ሀገራት ተስፋፍቷል። በአሁኑ ወቅት በዓለም…

በዓለም በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ30 ሺህ በልጧል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ30 ሺህ በለጠ፡፡ መነሻውን ቻይና ሁቤ ግዛት ያደረገው ኮሮና ቫይረስ አሁን ላይ የአለም ስጋት መሆኑን ቀጥሏል፡፡ በዚህም ከ170 በላይ ሃገራትን አዳርሷል፡፡ ይህ ዘገባ…

በዓለም በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 28 ሺህ ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2012( ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች  ቁጥር 28 ሺህ 717 መድረሱ ተገልጿል። በቅርቡ በቻይና የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ  አሁን ላይ የተለያዩ የዓለም ሀገራትን በማዳረስ  በርካታ ዜጎችን ለህልፈት እየዳረገ…

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪማሃማት ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በተደረገላቸው ምርመራ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸውን አስታወቁ። ሙሳ ፋኪ ማሃማት ከእሳቸው የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው የሥራ አጋሮች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ በትናንትናው ዕለት…

ዶናልድ ትራምፕ ጄኔራል ሞተርስ የመተንፈሻ መሳሪያ እንዲያመርት አዘዙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መኪና አምራቹ ጄኔራል ሞተርስ የመተንፈሻ መሳሪያ እንዲያመርት አዘዙ። ፕሬዚዳንቱ ጄኔራል ሞተርስ ለኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች የሚያገለግል የመተንፈሻ መሳሪያ እንዲያመርት ነው ትዕዛዝ ያስተላለፉት።…

ቦሪስ ጆንሰን በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በኮሮና ቫይረስ ተያዙ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደረገላቸው ምርመራ የቫይረሱን ምልክት ማሳየታቸውን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል። ቦሪስ ጆንሰን አሁን ላይ ራሳቸውን ማግለላቸውንም…

አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ዓለም ላይ ቀዳሚ ሆናለች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ በተያዙ ሰዎች ከዓለም ቀዳሚ ሃገር ሆናለች። አሁን ላይ በሃገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ85 ሺህ በልጧል። ይህም ዓለም ላይ ከፍተኛው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል። እንደ ጆንስ…

የኮሮናቫይረስን ለመግታት ሰዎችን እንቅስቃሴ መገደብ ብቻ ሳይሆን መለየትና መመርመር ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል- ዶ/ር ቴድሮስ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ሰዎችን እንቅስቃሴ መገደብ ብቻ ሳይሆን መለየትና መመርመር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አስታወቁ። ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ባስተላለፉት…

በዓለም በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 22 ሺህ ደርሷል

አዲስ አበባ ፣መጋቢት 17፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 22 ሺህ 30 መድረሱ ተገልጿል። በቅርቡ በቻይና ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አሁን ላይ 170 በሚሆኑ የዓለም ሀገራት ውስጥ መስፋፋቱ ተነግሯል።…

የዌልሱ ልዑል ቻርለስ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዌልሱ ልዑል ቻርለስ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተነገረ። የ71 አመቱ ልዑል በተደረገላቸው ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸውንና የቫይረሱ ምልክት እንደታየባቸው ከብሪታንያ ንጉሳዊ ቤተሰብ መኖሪያ የወጡ መረጃዎች አመላክተዋል። የ72 አመቷ…