Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠ/ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀን ለኔዘርላንድስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ገለጻ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለኔዘርላንድስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ገለጻ አደረጉ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከኔዘርላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስቲፍ ብሎክ ጋር የተወያዩት በስልክ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

አቶ ደመቀ በጁንታው ህወሓት የተፈጸመውን ክህደት እና ባለፉት ሦስት ሳምንታት ስለተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ አብራርተውላቸዋል፡፡

ይህ ህግን የማስከበር ዘመቻ በድል መጠናቀቁን የገለጹት አቶ ደመቀ በአድዋና በሌሎች አካባቢዎችም ውይይቶች እየተካሄዱ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡

አቶ ደመቀ አጥፊው ህወሓት ኤርፖርቶችን ጨምሮ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን እንዳወደመ ጠቅሰው አሁን የክልሉን ዕድገትና ልማት ለማስቀጠል መንግስት መልሶ ማቋቋም ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

እንዲሁም የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያሻቸው ዜጎች ከዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ተቋማት ጋር በመተባበር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በመጨረሻም አቶ ደመቀና የኔዘርላንድስ አቻቸው የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.