Fana: At a Speed of Life!

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለውጭ ንግድ ከቀረበ 300 ሺህ ቶን ቡና 1 ነጥብ 42 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለውጭ ንግድ ከቀረበ 300 ሺህ ቶን ቡና 1 ነጥብ 42 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል ።

በ2014 ዓ.ም ከታቀደው የቡና ምርት መጠን በ92 በመቶ አፈፃፀም 652 ሺህ ቶን መሰብሰብ ሲቻል ፤ ለውጭ ገበያ ከቀረበው 300 ሺህ ቶን ቡና ነው 1 ነጥብ 42 ቢሊየን ዶላር ገቢ የተገኘው፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት ገቢ አንፃር በ21 በመቶ ወይም በ48 ሺህ ቶን ጭማሪ ያለው ነዉ ተብሏል ።

ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ያልነበራትን አዲስ የቡና ብራንድ በ2014 በጀት ዓመት እንዲኖርና ብራንዱ በኢትዮጵያና በጃፓን እንዲመዘገብ መደረጉን የባለስልጣኑ ጄኔራል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ ተናግረዋል።

ይህም የኢትዮጵያ ብራንድ ቡና በእስያ ተቀላቅሎ እንዳይሸጥ ትልቅ አቅም ሆኗል ብለዋል።

በፀጋዬ ወንድወሰን

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.