Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ  4 ሺህ 400 ኩንታል የእርዳታ ስንዴ ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ግለሰቦች  በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ለተፈናቀሉ ወገኖች በእርዳታ የቀረበ 4ሺህ 400 ኩንታል ስንዴ አየር በአየር ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር የማነ ገሰሰው ÷ለተፋናቃዮች የመጣ የእርዳታ እህል ሰሞኑን አየር በአየር ለመሽጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ስምንት ሰዎች ተይዘዋል ብለዋል።

ግለሰቦቹን ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በተጠርጣሪ ግለሰቦቹ እጅ የነበረ የእርዳታ ስንዴን ለተፈናቃይ ወገኖች እንዲከፋፈል መደረጉን አመልክተዋል።

“ለተፈናቃይ ወገኖች የቀረበ  የእርዳታ  ስንዴ ዘርፎ ለግል ጥቅም ለማወዋል መሞከር  አፀያፊ ነው” ያሉት ሀላፊው፤  በእርዳታ የሚቀርብ እህል በአግባቡ ለተፈናቀሉ እንዲደርስ ሁሉም በንቃት ሊከታተል እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.