Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮው ክረምት 1 ነጥብ 3 ቢሊየን የቡና ችግኝ ለመትከል ታቅዷል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮው ክረምት 1 ነጥብ 3 ቢሊየን የቡና ችግኝ ለመትከል መታቀዱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ቡና አብቃይ በሆኑ ዞኖች አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ መሃመድ ሳኒ ገልጸዋል፡፡

ሃላፊው በጅማ ዞን እየተደረገ ያለውን የችግኝና የችግኝ ጉድጓድ ዝግጅት የተመለከቱ ሲሆን ፥ በዞኑ እየተደረገ ያለው ዝግጅት ተስፋ ሰጪና ለሌሎች አካባቢዎች ተምሳሌት እንደሚሆን ተናግረዋል።

ከቡና ልማት ጎን ለጎን በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ 4 ነጥብ 8 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱንም አቶ መሃመድ ሳኒ ጠቁመዋል።

የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ትጃኒ ናስር በበኩላቸው፥ በዞኑ በዘንድሮው ክረምት 455 ሚሊየን የቡና ችግኞች ለማልማት ታቅዶ አስፈላጊው ቅድመዝግጅት መጠናቀቁን ገልፀዋል።

በሙክታር ጠሃ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.