Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 1 ሺህ 161 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 282 የላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 161 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም በኢትዮጵያ እስከአሁን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 161 ሺህ 974 ደርሷል።

በ24 ሰዓታት ውስጥ 364 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 136 ሺህ 443 ሆኗል።

እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮና ቫይረስ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 23 ሺህ 138 ሰዎች መካከል 398 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.