Fana: At a Speed of Life!

አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ በበጀት ዓመቱ ከ1ቢሊየን በላይ አረቦን ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ በበጀት ዓመቱ 1 ነጥብ 28 ቢሊየን አረቦን መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
ኩባንያው በዚህ ዘርፍ የ23 በመቶ የሽያጭ ገቢ እድገት አስመዝግቧል ነው የተባለው፡፡
በሕይወት መድን ስራ ዘርፍም ከ332 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ አረቦን ገቢ በማግኘት የ 181 በመቶ ዕድገት ያስመዘገበ ሲሆን ÷በሁለቱም የሥራ ዘርፎች በድምሩ 1 ነጥብ 28 ቢሊየን የአረቦን ገቢ በመሰብሰብ የ44 በመቶ አጠቃላይ የገቢ ዕድገት አስመዝግቧል፡፡
ላሰመዘገበው እድገትም ላለፉት 26 ዓመታት አብረውት ለዘለቁ ደንበኞቹ ምስጋና አቅርቧል፡፡
በሌላ በኩል ኩባንያው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የደንበኞች ፍላጎት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ሠላም ተካፉል የተሰኘ የሸሪአ ሕግን ያማከለ የኢንሹራንስ አገልግሎት ለተገልጋዮች መስጠት መጀመሩን ገልጿል፡፡
ኩባንያው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አገልግሎቱ በክልል ከተሞች በሚገኙ 10 ቅርንጫፎቹ እየተሰጠ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.