Fana: At a Speed of Life!

ክልሉ ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት ሹመት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስድስት አባላት ሹመት መስጠቱን አስታወቀ፡፡
በክልሉ ለሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት ዛሬ የተሰጠው ሹመት÷ ስድስተኛ ጠቅላላ ምርጫ በክልሉ ሙሉ በሙሉ ተካሂዶ መንግስት እስኪመሰረት ድረስ የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ነው ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን ገልጸዋል፡፡
በዚህም ከቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ (ቤህነን) አቶ አብዱሠላም ሸንገል የክልሉ መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ እና ከቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ቦዴፓ) አቶ አመንቴ ገሺ የክልሉ መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ ሆነው መሾማቸውን አስታውቀዋል።
እንዲሁም ከቤህነን ፓርቲ አቶ መርቀኔ አዙቤር የክልሉ ዳያስፖራ ጽህፈት ቤት ሃላፊ እና አቶ መሃመድ እስማኤል ደግሞ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ፣ ከቦዴፓ ፓርቲ ደግሞ አቶ መልካሙ ጅራ የመተከል ዞን ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሃላፊ ሆነው መሾማቸውን አስረድተዋል፡፡
ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ተቀራርቦ መስራት ህዝብን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ብልጽግና ፓርቲ ያምናል፤ የሹመቱ ዓላማም ይኸው ነው ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.